መንግስት የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ ቁልፍ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ አድርጎ እየሰራበት ይገኛል፡ የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን 3ኛውን ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ካደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፤

 • ሃገራችን ሳይበር ቴክኖሎጂ ለእድገታችን ስኬት ዋነኛ አውታር መሆኑን በመረዳት ከ10 አመቱ የልማት እቅድ ከዋና ዋና ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ አድርጋ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡
 • የሳይበር ጥቃት የአለማችን የወቅቱ የሥጋት ምንጮች ከሚባሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡

 • መንግስት የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ ቁልፍ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ አድርጎ እየሰራበት ይገኛል፡፡
 • በሳይበሩ ዘርፍ የመወዳደሪያ አቅምና ተስፋችን በታዳጊ ወጣቶች ላይ በመሆኑ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና መሰል ተቋማት ውስጥ ታዳጊዎችን በዘርፉ ኮትኩቶ ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕከላት ተቋቁመው አመርቂ ውጤት ማሳየት ጀምረዋል፡፡

 • ዲጂታል 2025 ኢትዮጵያን ቀርጸን በብዙ ዘርፎች ላይ መተግበር ጀምረናል፡፡ ይህ ትልም ለብልጽግና ጉዟችን አስቻይ እንዲሆን ከቴክኖሎጂ ልማት እኩል ለደህንነቱም ትኩረት መስጠት ይኖርብናል፡፡
 • ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ብሎም የሳይበር ደህንነትን እውን ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝ ነው፡፡
 • የሃገራችንን የሳይበር ደህንነት የማረጋገጥ ሥራ በዋነኝነት ለኢንፎርሜኝ መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠ ቢሆንም ያለሁላችን ተሳትፎ ውጤታማ ሊሆን ስለማይችል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡
 • ዛሬ በተዘጋጀው የሳይበር ደህንነት ወር ላይ የተገኘን ባለድርሻ አካላት ቅንጅታችንን የምናጠናክርበት፣ በጋራ አላማ ላይ በመመስረት መተባበር እንድንችል ምቹ አጋጣሚን የሚፈጥር መድረክ በመሆኑ በውጤታማነት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

የሃገራችን ሉዓላዊነት አንዱ መገለጫ የሳይበር ምህዳሩ እንደመሆኑ መጠን በዘርፉ ከሌሎች ሃገራት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራት ይኖርብናል፡፡ ከዚህ አኳያ የሳይበር ዲፕሎማሲ ሥራችንን በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራበት መስክ መሆኑ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች