ኢመደአ ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ሥራ የሚያኮራ ነው - ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
ኢመደአ ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ሥራ የሚያኮራ ነው - ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ የሚያከናውናቸው የምርምርና ልማት ሥራዎች እንደ ሃገር ትልቅ ኩራት የሚፈጥሩ እንደሆነ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ የቀረቡ የኢመደአ ምርትና አገልግሎቶችን ተመልክተዋል፡፡
በኢመደአ የቀረቡ ምርቶችና አገልግሎቶች የመንግስትን አሰራር በማዘመንና ቀልጣፋ በማድረግና ይህም ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ በኩል ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ ጎብኚዎቹ ገልጸዋል፡፡
ኢመደአ በሳይንስ ሙዚየም ለሕዝብ እይታ ያቀረባቸው ምርትና አገልግሎቶች በተቋሙ አቅም የተሰሩና የሃገራችንን የቴክኖሎጂ ባለቤትነት የማረጋገጥ ጉዞ የሚያሳዩ ሲሆን፤ የሳይበር ጥቃትን በመከላከልና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል የሚሰሩ ሥራዎችንም አካቶ ይዞ ቀርቧል፡፡