ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነትና ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ጉባኤ በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነትና ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ጉባኤ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ማህበር አዘጋጅነት በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ላይ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሀገራዊ የሳይበር ሥነ-ምህዳር ለማጠናከር ይህን መሰል መድረኮች ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገር እቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃቶችና ተጋላጭነቶች ከአመት ወደ አመት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ከፍ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በይበልጥ በዘርፉ ከተሰማሩ እንደ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ማህበር ጋር በትብብር ይህን መሰል ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀታችን በዘርፉ እንደሃገር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የገለጡት ወ/ሮ ትዕግስት ዘርፉን ለማጠናከር መሰል ተቋማትን መደግፍና ማበረታታት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ይሽሩን አለማየሁ እንደገለፁት ፤የ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማስተግበር በዘመናዊ የዲጂታል ሽግግር የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

የጉባኤው ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ሐገራዊ የሳይበር ሥነ ምህዳር (Eco-system) ለማጠናከር የሚያስችል የውይይት መድረክ ነው፡፡ በዘመናዊ የዲጂታል ሽግግር በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር የሚደረግ ሲሆን፣ የፖሊሲ ግብአቶችን ለማቀድ የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

ጉባኤው ከየካቲት 26 እስከ 27/2016 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሳይበር ደህንነት፣ የሳይበር ህግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከ12 በላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።