ተቋማቱ 16ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በጋራ አከበሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቋማት አመራር እና ሠራተኞች 16ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም ለአራቱም ተቋማት አመራርና ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ባስተላለፉትበት ወቅት እንደተናገሩት ሰንደቅ አላማ በአንድነት የሚያስተሳስር ገመድ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም አርበኞች ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰውና ውድ ሕይወታቸውን ገብረው ያቆዩት እንደመሆኑ መጠን የሉዓላዊነታችን ምልክት፣ የነፃነታችን አርማና የክብራችን መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም አያይዘው እንደተናገሩት አርበኝነት ከተጋድሎ ባሻገር በተለያየ መንገድ የሚገለጽ መሆኑን ገልጸው፤ አትሌቶቻችን በተለያየ ስፖርታዊ መድረክ የሀገራችንን ስሟን እንዳስጠሩ፣ ባንዲራውንም ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እንዳደረጉ ሁሉ የዚህ ዘመን ትውልድም ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና በምታደርገው ግስጋሴ የበኩሉን የአርበኝነት ተጋድሎ ማድረግ እንደሚጠበቅበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተርን ወክለው መልእክት ያስተላለፉት የኢመደአ ፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ደረጀ መኮንን በበኩላቸው ለመላው የተቋማቱ አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በማስተላልፍ፤ ባንዲራ የአንድነት፣ የሰላም፣ የክብርና የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑን አስረድተው መጪው ጊዜ የሠላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ብዙዎች የሕይወት መስዋዕት የከፈሉለት፤ በዓለም መድረኮች በክብር የተዘመረለትን ሰንደቅ ዓላማ በማክበር የታሪክ ተካፋይ ስለሆንን ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች