የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጋር የስራ ውል ስምምነት ተፈራረመ
የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጋር የስራ ውል ስምምነት ተፈራረመ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጋር በዛሬው እለት የስራ ውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት እንደሆነ በፊርማ ሥነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
ሰምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል ፈርመዋል፡፡
በውል ስምምነቱ ወቅት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንዳሉት ኢመደአ የፋይናንስ ሴክተሩን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥና አጠቃላይ ዘርፉ ለዲጂታል የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያደርገውን አስተዋጻኦ ከመደገፍ አኳያ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም እንዲያስችለው የሳይበር ደህንነቱን በቀጣይነት የማረጋገጥ ሥራ ለመስራት ስምምነቱ አስቻይ እንደሆነ ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዋዕለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል በበኩላቸው ተቋማቸው ከተቋቋመ አጭር ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢመደአ በሳይበር ደህንነት እንዲሁም ቴክኖሎጂ ልማት ያካበተውን እምቅ አቅም በመጠቀም ውጤታማ ስራዎች እንደሚሰሩ ያላቸውን አምነት ገልጸዋል፡፡