ኢመደአ የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ የሃገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት ያስከብራል - የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ፕሮግራም እንዲሁም “ሥውር ውጊያ” የፊልም ምርቃት መርሃ ግብር ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ ሀገር በቀል የሆኑና የዲጂታል 2025 የሚደግፉ ቴክኖሎጂዎች በማልማት፣ ሀገራዊ የሳይበር ሀይል ለመፍጠር ደግሞ አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ ስልጠናዎችን አባላቱ እንዲያገኙ በማድረግና በሳይበር ታለንት ልማት ማዕከሉ ባለ ልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን ተሰጥዎቻቸዉን በማሳደግ ፈርጀ ብዙ ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ሀገር አሁን ባለንበት ዘመን የተቋማትን መረጃዎች፣ የመረጃ መሠረተ ልማቶችንና ሥርዓቶችን ከሳይበር ሥጋት፣ ተጋላጭነት እና ጥቃት መከላከል የሚያስችል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ብቃት ያለው አገራዊ የሳይበር ኃይል መገንባት አስፈላጊ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህን እዉን ለማድረግ የቴክኖሎጂና የእዉቀት ባለቤትነት ማረጋገጥ፣ ብቁ የሳይበር ሰራዊትና በሳይበር ደህንነት ላይ ንቃተ ህሊናዉ ከፍ ያለ ማህበረሰብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ አኳያ በዛሬው እለት የተመረቀዉና በእዉነተኛ ኹነት ላይ የተመሰረተዉ ፊልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ፤ በሀገራችን ደግሞ ለ4ተኛ ጊዜ “አይበገሬ የሳይበር አቅም ለአገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚከበረዉ የሳይበር ደህንነት ወር “ልዩ ገጸ በረከት” ሆኖ የቀረበ እንደሆነ አቶ ሰለሞን ሶካ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በመጨረሻም ባስተላለፉት መልእክት ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ4ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አደረሳችሁ በማለት ሁሉም ዜጎች ከጥቅምት 12 እስከ ጥቅምት 15/2016 ዓ/ም ድረስ በግዮን ሆቴል ለእይታ ክፍት የሚሆነዉን የሳይበር ደህንነት ዓውደ ርዕይ እንዲጎበኙ እንዲሁም በወሩ በሚከበሩ ሌሎች ኩነቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ግብዣቸውን አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች