የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ፡፡ ክብርት ዋና ዳይሬክተሯን ጨምሮ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሀገርን ሰላምና የሕዝን ደህንነት በማረጋገጥ ወንጀልን የመከላከል ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ እና ለዚህም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን የዲጂታላይዜሽን እድገትን ተከትሎ ከመደበኛ ወንጀሎች ባሻገር የሳይበር ሥነ ምህዳርን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤  በአንድ በኩል እነዚህን ወንጀሎች በብቃት ለመከላከል፤ በሌላም በኩል የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል አቅም ለመገንባት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሃይል ልማት፣ በጥናትና ምርምር፣ በትምህርትና ስልጠና ወ.ዘ.ተ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ አቅጣጫ መቀመጡን ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሀገራችን ሰላምና የህዝቦችን ደህንነት እንዲሁም የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ፤ ወንጀል በማንኛውም ሁኔታ እንዳይፈጸም ለመከላከል በሁሉም አካባቢዎች የሠራዊቱ አባላትን በማሰማራት ሌት ተቀን ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የሀገራችንን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች የሀገሪቱ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በትብብርና በቅንጅ መስራት ወሳኝ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር ደህንነት፣ በቴክኖሎጂ ልማት፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ረገድ ያካበተውን ሰፊ እውቀትና ልምድ በመጠቀም የዩኒቨርሲቲውን ሁለንተናው አቅም ማጎልበትና ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ ማስቻል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ተስፋዬ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮ ለመደገፍ የሚያስችሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርትና አገልግሎቶችን ለማስታጠቅ ኢንስቲትዩቱ ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን የስራ ጉብኝት ማድረጋቸዉ ይታወሳል፡፡  

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች