ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ምዝገባ ተጀመረ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) 2016 /ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅፕሮግራም ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አደረገ፡፡

በኢመደአ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ በዛሬው እለት ለጋዜጠኖች በሰጡት መግለጫ 2016 /ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅፕሮግራም ምዝገባ ከግንቦት 15/2016 እስከ ግንቦት 30/2016 / ድረስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በሐገር አቀፍ ደረጃ ምልመላው ለዚሁ ፕሮግራም ተብሎ በተዘጋጀ ፖርታል https://talent.insa.gov.et  እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

አለም እየተመራች ካለችበት እጅግ ተለዋዋጭና ውስብስብ የሳይበር ምህዳር አንፃር በሳይበር ደህንነት መስክ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በየደረጃው ማነቃቃት፣ መመልመል፣ ማልማትና መጠቀም አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ የገለጹት አቶ ቢሻው፤ ከዚህ አኳያ ኢመደአ በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በማልማት እና በዘርፉ እንደ ሐገር ያለውን ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በመቅረፍ ረገድ የሚጠበቅበትን ሚና እየተወጣ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 2014 በጀት አመት እና 2015 በጀት አመት ለሁለት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በክረምት ፕሮግራም (Summer Program) አሰልጥኖ ማስመረቁን ያስታወሱት አቶ ቢሻው፤ ተመራቂዎችንም እንደየችሎታቸውና እንደስራዎቻቸው ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር የማስተሳሰር፤ ኢመደአን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ተቀጥረው መስራት የሚችሉበት ሁኔታም ተመቻችቷል ብለዋል፡፡

ይህንንም መነሻ በማድረግ ባለፉት ሁለት አመታት የተከናወኑ የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራሞችን መነሻ በማድረግ 2016 በጀት አመትብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅፕሮግራም መዘጋጀቱን አቶ ቢሻው ገልጸዋል፡፡ የዚህ ቻሌንጅ ዋና ዓላማም በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ መስኮች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸዉን ሰዎች በመመልመል በዘርፉ ላይ ተጨባጭ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ብሄራዊ የሳይበር ሰራዊት (National Cyber Army) መገንባት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው እና እድሜያቸው 11 አመት ጀምሮ ያሉ ኢትዮጵያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ አቶ ቢሻው በየነ ገልጸዋል::

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች