የኢመደአ አመራርና አባላት የአለም አቀፉን የወጣቶች ቀን አከበሩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራርና አባላት “ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን አከበሩ።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ24ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ “ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ቃል ለሚከበረዉ የወጣቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መሪ ቃሉ ወጣቶች በዲጂታል ቴከኖሎጂ ላይ ሚኖራቸውን አስተዋጾ ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት መሰረት እንዲሆን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ እለቱን ስናከብር ወጣቶች ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ትስስር እንዲጎለብቱ በመደገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል

የወጣቶችን ተሳትፎ ከሚያሳድጉና በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ይፋ የተደረገዉ የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭም አንዱ የመንግስት ከዲጂታል ምህዳሩ ላይ የወጣቶችን ሚና ከፍ ለማድረግና የኢኮኖሚ ተጠሚነታቸዉን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ትዕግስት ሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች በኢኒሼቲቩ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። ኢመደአ እንደ ተቋም ለመርሃ-ግብሩ የሚሆኑ ፕላትፎርሞች ደህንነት ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ፣ ማስፋፊያዎችን የመስራት፤ የኢንተርንሽፕ እድሎችን የማመቻቻት እንዲሁም ተጨማሪ የስልጠና መርሃ-ግብሮችን እና ይዘቶችን በመፍጠር ተደራሽ የማድረግ ሚናዉን እንደሚወጣ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

እንደ ሃገር መንግስት ለዲጅታላይዜሽን የሰጠውን ትኩረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በታለንት ልማት ማዕከል በኩል ወጣቶችን በመመልመል ለሃገራቸው ልማት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱ እና እየሰራ ንደሆነ ዋና ዳይሬክተሯ አክለው ገልፀዋል፡፡

ወጣቶች የዚች ገር ትልቅ ተስፋ መሆናችሁን አምናቹ ከምታዩት እና ከምትሰሙት ያዊ ነገር ወጥታችሁ የሚጠቅማችሁ መምረጥ እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀማችሁን ጥንቃቄ የተሞላበት በማድረግ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ብዙ ነገር ማቅለልና መተግበር የምትችሉበትን አቅም መፍጠር ይጠበቅባችኋ ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ለወጣቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሯ በዚሁ መድረክ ላይ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻና መደበኛ ትምህርቶችን በነጻ እና የዋጋ ቅናሽ በማድረግ ለተቋሙ አባላት የትምህርት እድል ለሰጡ አካላት የእዉቅና ሰርተፍኬት ሰተዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች