ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

Nested Applications

Asset Publisher

ኢመደአ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ2018 አዲስ ዓመትን በማስመልከት ድጋፍ አደረገ።

ኢመደአ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ2018 አዲስ ዓመትን በማስመልከት ድጋፍ አደረገ። Fri, 5 Sep 2025

ድሮን አምርቶ እስከ መታጠቅ

ድሮን አምርቶ እስከ መታጠቅ Fri, 5 Sep 2025

እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Fri, 5 Sep 2025

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የገነባችው አቅም በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የገነባችው አቅም በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ ተገለጸ Fri, 29 Aug 2025

Asset Publisher

null ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገለጹ።

ይህን ያሉት ኢትዮጵያ በብራዚል መዲና ብራዚሊያ በተካሄደው የብሪክስ የሳይበር ደህንነት እና ጥበቃ ስብሰባ ላይ በተሳተፈችበት መድረክ ላይ ነዉ።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ምህዳር ለመፍጠር ሀገር አቀፍ ትብብር እና ዓለም አቀፍ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በስብሰባው ላይ ስለ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ገለጻ አድርገዋል።

ፖሊሲው የመንግስት፣ ህዝብ እና የበርካታ ባለድርሻ አካላት የጋራ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ፣ ለቁልፍ የመረጃ መሰረተ ልማቶች እና ለግል መረጃ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም ለዲጂታል የኢኮኖሚ ተግባራት ደህንነቱ የጠበቀ አሰራርን መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነት እንዲጠናከር ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

በብሪክስ ማዕቀፍ አማካኝነት በኢንፎርሜሽን ደህንነት ዘርፍ እድሎችን መጠቀም እና ስጋቶች በጋራ መከላከል እንደሚገባም ነው አምባሳደሩ ያሳሰቡት።

ስብሰባው የብሪክስ አባል ሀገራት የአይሲቲ ደህንነት ይዞ የመጣቸው እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ሀሳቦችን እንዲለዋወጡ እና ሀገራዊ ተሞክሯቸውን እንዲያቀርቡ ምቹ አጋጣሚን መፍጠሩ ተመላክቷል።

አባል ሀገራቱ በጉዳዩ ላይ ብሪክስ ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተመላክቷል።