የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ 

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሠረተ-ልማት ደህንነት መጠበቅ ኃላፊነቱና ተልእኮው እንደመሆኑ መጠን ለመንግስት ቁልፍ ተቋማትን 24/7 የደህንነት ጥበቃ ከማድረግ ባሻገር ክልከላ ያለባቸውን ሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮችን አበልጽጎ የማስታጠቅ ሥራን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

   

ክቡር አቶ ሰለሞን አያይዘውም ዛሬ ከኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ጋር የተደረገው ሥምምነት የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ፣ 24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎት፣ የሳይበር ደህንነት ኦዲት፣ አገልግሎቱ ያሉበትን የሳይበር ደህንነት ሥጋትና የተጋለጨነት ክፍተቶችን የመለየትና የመድፈን ስራዎችን በመስራት ተቋሙ የጀመረዉን በቴክኖሎጂ የመዘመን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ጠቁመዋል።

በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ኢመደአ ለኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር / ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ከኢመደአ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸው እንዳስደሰታቸዉ በመግለጽ፣ ተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ተቋሙ በባህሪው የሚይዛቸው መረጃዎች ሚስጥራዊነት እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከኢመደአ ጋር መሥራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ወደፊት በርካታ ሥራዎችን በጋራና በትብብር እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች