"ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ “የፅናት ቀን” በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ተከናወነ።
"ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ “የፅናት ቀን” በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ተከናወነ።
"ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ የጸጥታና ደህንነት ተቋማት በጋራ ያዘጋጁት የፅናት ቀን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተለያዩ መርሐ-ግብሮች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙትና መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እንደገለጹት ለዘመናት የሀገራችንን ክብር እና ማንነት ማስጠበቅ የቻልነው በማይናወጥ ፅናታችን ነው ብለዋል።
ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጽናት የሚለዉ ቃል ከፅንሰ ሀሳብ በላይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ የታሪካችን የልብ ትርታ፣ የማንነታችን መገለጫ እና በአጠቃላይ የኑሮ ዘይቤያችን አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያውን ዛሬ የምናከብረው የፅናት ቀን ያለፉትን ድሎች የምናስብበት ብቻ ሳይሆን የወደፊቱንም ተስፋዎች የምንቀበልበት ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዉ ቀኑን የምናከብረው፤ ከፅኑ መንፈሳችን የተወለዱትን ድሎች በማደስ፣ በእያንዳንዷ ፈተና ውስጥ የማሸነፋችንን እና የማለፋችንን እውነት እንድንረዳ እንዲሁም ከእኛ በፊት የነበሩ ጀግኖች ለከፈሉት መስዋዕትነት ክብር ለመስጠት ነው ብለዋል፡፡
ያስመዘገብናቸው እመርታዎች የጸጥታ እና የደህንነት ተቋሞቻችንን ከማዘመን ጀምሮ እስከ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን መሆን የአንድነታችን፣ የጋራ ዓላማችንና ያላሰለሰ ፅናታችን ውጤት ማረጋገጫ መሆናቸዉን ያነሱት የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ የፅናት ቀን አንድነታችንን፣ ጥንካሬያችንን እና ኃይላችንን በማደስ ነገን የበለጠ ብሩህ ለማድረግ የማያወላውል ቃላችንን የምናንፅበትም እለት መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የጽናት ቀን በጧፍ የማብራትና ቃል ቃለ መሃላ በመግባት ተጠናቋል።