ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለኢመደአ ሰራተኞች እና ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን ለ2018 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

አዲስ ዓመት ደስ የሚል፣ ወደ ተስፋና ብርሃን የምንሄድበት በዓል በመሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ትልቅ በዓል ነው። ሁሉም በደስታ የሚያከብረውና ጓጉቶ የሚጠብቀው በዓልም ነው ። ምክንያቱም የሁለት ወራት የክረምት ወቅት አሳልፈን ወደ ፀደይ እና ወደ ብርሃን የምንሻገርበት ወቅት በመሆኑ ካሉት በዓላት ሁሉ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ነው። አዲስ ዓመት ሲመጣ የአብሮነት፣ የጸሎት፣ የተስፋ እና የመልካም ነገሮች ምኞት ወቅትም ነው፡፡

የ2018 አዲስ አመት ከሌላው ጊዜ የሚለየው በ2017 ዓ.ም የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በህዝባችን እና በመሪዎቻችን ብርቱ ትጋት በላብና በደም ጠብታ ገንብተን አጠናቀን ያስመረቅንበት እንዲሁም በአጠቃላይ በኢኮኖሚው እና ዲፕሎማሲው ዘርፍ ድል ያስመዘገብንበት ለህዝባችን ተጨባጭ ስኬቶችንም ያስመዘገብንበት ዓመት መሆኑ ነው::

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት እንደሚያስጠብቅ ተቋም በሀገራችን ዲጂታል ምህዳር ላይ የሳይበር ጥቃት እንዳይደርስ 24/7 በከፍተኛ ሀገራዊ ሃላፊነት እየሰራ ይገኛል::

አዲሱ አመት ለኢትዮያዊያን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሻገርበት የማንሰራራት ዘመን ከሚታይ ህልም ወደ ሚጨበጥ ስኬት የሚያሻግር ብሩህ ዘመን የሚሆንበት ፤ መተጋገዝና ትብብር የሚሰፍንበት፣ ጥላቻን የምናርቅበትና አንዳችን ለሌላችን መከታ ከለላ የምንሆንበ እና እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደፊት የምንሻገርበት ዓመት ይሁንልን::

በዚህ አጋጣሚ በበዓላት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትና ግብይት እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ የሚፈጸም በመሆኑ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ የሳይበር ወንጀለኞች እንደ ምቹ አጋጣሚ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በበዓላት ወቅት ከሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እራሱን እንዲጠብቅ ለማስታወስ እወዳለው፡፡

በመጨረሻም መጪው 2018 አዲስ አመት ለመላ ኢትዮጵያውያን እና ለኢመደአ ሰራተኞች የሰላም፣ የፍቅርና፣ የመተሳሰብ ዓመት እንዲሆንል እመኛለሁ::

መልካም አዲስ ዓመት