˝ዲጂታል ቅኝ ግዛት” እና የሚያስከትለው ተጽእኖ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

˝ዲጂታል ቅኝ ግዛትጽንሰ ሃሳብ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊ ግዛት በስዉርም ሆነ በግላጭ ያለ ፍቃድ

ጥሶ በመግባት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የበላይነት የመቆናጠጥ እንቅስቃሴ ነው።

በቀድሞዉ የቅኝ ግዛት እሳቤቅኝ ገዥነትበሌሎች ሀገራት ዉስጥ በመግባት እና በሀገራቱ ዉስጥ ያሉ ወሳኝ መሠረተ-ልማቶችንና ተቋማትን የመቆጣጠርና በባለቤትነት በመያዝ የሰዉ ሃይልን፣ ዕውቀትን እና ሸቀጣ ሸቀጦችን የመበዝበዝ ተግባር ነዉ። በዚህ ሂደት ዉስጥ የሀገራቱን ሥልጣንን ወሰን እንደ እራስ በመጠቀም ዜጎችን በጭቆና ቀንበር ማዋል ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ዓይነቱ የብዝበዛ ሂደት ለብዙ መቶ ዘመናት በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ሲሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፈጠር ደግሞ ጉዳዩን ወደ ድብልቅ ቅኝ ግዛት እሳቤዎች እንድንገባ አድርጎናል።

ዲጂታል ሉዓላዊነት ጽንሰ ሀሳብ ዲጂታል መለኪያን እንዲይዝ ያደረጉት የግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አዳጊ ሀገራት ሊቋቋሟቸዉ በማይችሉት መልኩ ተጽዕኗቸዉ እጅግ መጨመሩን ተከትሎ ነዉ። ለዚህ እንደ ትልቅ ማሳያ መዉሰድ የሚቻለዉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ማለትም ጉግል፣ ሜታ (ፌስቡክ) አፕል፣ አማዞን እና ማይክሮሶፍት ዓለም አቀፍ ተጽኖዋቸውን ማየት በቂ ነዉ።

በዲጂታል ምህዳሩ ላይ ምህዳሩን በመግራትና በመምራት ቀዳሚ የሆኑ ሀገራት የቴክኖሎጂ የበላይነታቸዉን በመጠቀምም በአዳጊ ሀገር መንግስታት ላይ በተራቀቁ መንገዶች ክትትሎችን እና ቁጥጥሮችን በመከወን ሉዓላዊነታቸዉን እየገፈፉ እና እየተጋፉ ይገኛሉ።

ሆኖም ይህ አይነቱ የዲጂታል ሉዓላዊነት ጥሰት ለአንዳንዶች አዲስ ሊመስል ቢችልም ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ በቴክኖሎጂ የበለጸጉ ሀገራት በአዳጊ ሀገራት በስዉርና በህገ-ወጥ መንገድ የዉስጥ ጣልቃ ገብነት በመፍጠር እና በመሰማራት  ˝ዲጂታል ቀኝ ግዛት˝ እሳቤ ስር ሰዷል።

እነዚህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችም የሳይበር ምህዳሩ ከፈጠራቸዉ መልካም እድሎች በተጻራሪ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የተጋረጡ አዳዲስ ተግዳሮቶች ናቸዉ።

እንደ ኢትዮጵያ አይነት ገና ወደ ዘርፉ እየገቡ ያሉ ሀገራት ከቴክኖሎጂ ልማት መሳ ለመሳ ጠንካራ የሆነና እነዚህን ሃገራት መገዳደር የሚችል ጸረ-ዲጂታል ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ማከናወን ካልተቻለ ሁኔታው ወደፊት በጣም የከፋ ሆኖ ይመጣል።

በመሆኑም መንግስታት የእነዚህን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሀገራትን ተጽእኖ ለመቀነስ እና የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከአጠቃላይ በጀታቸዉ የተወሰነዉን በግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ሊያዉሉት ይገባል።

ከዚሁ ጎን ለጎን የዲጅታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ አዲስ የሆነ አካሄድን መከተል የሚያስፈልግ ሲሆን ፈጠራን ማበረታታት፣ ለድርድር ሊቀርቡ የማይችሉ በራስ ቴክኖሎጂ የመከላከል ብቃትን መፍጠር፣ ዘላቂነት ያለዉ ቴክኖሎጂ ማበልጸግ እና ራስን የሚያስከብር አቅም መፍጥር መሰረታዊ ጉዳይ ነዉ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ተቋም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት እንዲያስጠበቅ በመንግስት ሃላፊነት የተጣለበት በመሆኑ አቅም ባልተፈጠረባቸዉ እና ክልከላ ባለባቸዉ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የሀገሪቱን የሳይበር ምህዳር ደህንነት ማረጋገጥ ላይ የጀመረዉን ሁሉን አቀፍ ስራ ማስቀጠል ይገባል።

ከዚህ ባሻገር ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በራስ አቅም በመታጠቅ የሰለጠነ የሰው ሃይል ባለቤት መሆን አለባት፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የዲጂታል ምህዳሩን በብቃት የሚቃኙ የቁጥጥር ማዕቀፎች የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት የማስጠበቅና እንዲሁምየዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ ስኬት መደላድል ለመፍጠር እያደረገ ያለዉን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉ ተገቢ ነዉ። ከሁሉም በላይ የዉስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም ካልተቻለ ችግሩ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ የዲጂታል ምህዳሩን ስፋት፣ ጥልቀት እና እውቀት መሰረት ባደረገ መልኩ ንቁ ተዋናይ መሆን ካልተቻለ አዳጊ ሀገር  የልዕለ ሃያላን መፈንጫ ከመሆን አያመልጡም።

 ከዚህ በመለስ ባህል ወረራን ጨምሮ ሀገራዊ ማህበረሰባዊ ክብርን በማሳጣት ለዲጂታል ቅኝ ግዛት ይዳርጋል።

ስጋቱን ለመቀነስ ኢትዮጵያም የዲጂታል ኢንደስትሪውን የራስ እውቀትን መሰረት ያደረገ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በፍጥነት ማረጋገጥ፣ የምህዳሩን ባህርይ መቋቋም የሚችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እና  ልማት ላይ ከፍተኛ ንዋይ ማፍሰስ ነገን ዛሬ ላይ መስራት ነው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከአውታረ-መረብ ሽፋን፣ ከዋጋ እና ጥራት ጋር የተያያዙ ጉድለቶች ባሉባቸዉ ሀገራት ህግን መሰረት ያደረጉ ትብብሮች በሀገሪቱ ያለዉን ዝቅተኛ የአጠቃቀም ሁኔታን ለመቅረፍ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። በተሟላ መልኩ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ደግሞ ሀገራዊ ፈጠራዎችን ማበረታታት እና መደገፍ ይገባል። በተለይ እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት አስተዳደር ያሉ ተቋማት በዘርፉ ካላቸዉ የሰዉ ሃይል ብቃት እና ልምድ አንጻር ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸዉን ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ሚናቸዉን

በአግባቡ መወጣታቸዉ ሀገር በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ልትደርስባቸዉ ላሰበችዉ የልማት እና ብልጽግና ትልም ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች