የኬንያ የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ልዑክ በኢመደአ ጉብኝት አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኬንያ ብሔራዊ የደህንነት አገልግሎት የውጭ ደህንነት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፍ ሳሊም ሱለይማን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎበኘ፡፡

ልዑካን ቡድኑ በኢመደአ በነበረው ጉብኝት በሳይበር ደህንነት እና ሳይበር ቴክኖሎጂ ልማት ዙሪያ ኢመደአ እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ሥራዎችን እንዲሁም የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ተመልክቷል፡፡

በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያለውን የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ ኢመደአ ከታዳጊ ሕጻናት ጀምሮ እየሰራ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑ የገለጹት ልዑካን ቡድኑ በእው ሃይል ልማት እንዲሁም በቀጠናዊ የሳይበር ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው የሳይበር ደህንነትን ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ የጋራ ስምሪቶች ዙሪያ የተለያዩ ምክክሮችን እንደሚያደርግም ይጠበቃል።