ኢመደአ ከኢትዮ-አሜሪካ ቻንበር ኦፍ ኮሜርስ አባላት ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረገ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከኢትየ-አሜሪካ ቻንበር ኦፍ ኮሜርስ አባላት ጋር በጋራ በሚሰሩበት ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይታቸዉ ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ኢትዮጵያ በያዘችው 10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ አንዱ የሆነው ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንዲያደረጉ ለትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮ-አሜሪካ ቻንበር ኦፍ ኮሜርስ አባላት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በምታደርገው የቴክኖሎጂ እውቀት ባለቤትነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር ሉዓላዊነት ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ የበኩላቸው ሚና እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡት ዋና ዳይሬክተሩ በሳይበር ታለንት ልማት መዕከልም የሚገኙ ባለ ልዩ ተሰጦ ታዳጊዎችን በመደገፍ አብረዋቸው እንዲሰሩ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት ሃሚድ በበኩላቸው በሳይበር ደህንነት እና ልማትና ምርምር መስኮች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ልምዳቸውንና ሃብታቸውን በመጪው ትውልድ ላይ ኢንቨስት ሊያደርጉ እንደሚገባቸው በውይይታቸው ወቅት ገልፀዋል፡፡ መንግስት ብቻውን ሁሉን ማድረግ እንደማይችል ሁሉ እናንተም የነገው ትውልድ ላይ በመስራት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ልታደርጉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮ-አሜሪካ ቻንበር ኦፍ ኮሜርስ አባላት በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ታለንት ልማት መዕከል በትውልድ ላይ እየሰራ ያለው ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ባለቤትነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት መደሰታቸውን ገልጸው ወደፊት አስተዳደሩ የሳይበር ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ በሚሰራቸው ዘርፎች ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

አያይዘውም ታዳጊዎች ላይ መስራት ቀጣይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሻራ ማስቀመጥ መቻል ነው ያሉት አባላቱ በቀጣይም የታለንት ማዕከል ያሉትን ባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮ-አሜሪካ ቻንበር ኦፍ ኮሜርስ አባላት ከዉይይታቸዉ ጎን ለጎን የተቋሙን ዋና መ/ቤትን የጎበኙ ሲሆን፡ በጉብኝታቸውም በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን ሀገር በቀል የሳይበር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና የታለንት ማዕከልን ጎብኝተዋል።